ዝርዝር ማውጫ

የ አገባብ ዝርዝር በ ሰንጠረዥ ማጠራቀሚያ ውስጥ የሚያቀርበው የ ተለያዩ ተግባሮች ነው እርስዎ ዳታቤዝ ሰንጠረዥ ውስጥ መፈጸም የሚችሉት: የ ተለየ ሰንጠረዥ ለማረም ከ ዳታቤዝ ውስጥ: ይምረጡ ተመሳሳይ ሰንጠረዥ እና ይክፈቱ የ አገባብ ዝርዝር

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ከ ዳታቤዝ ፋይል መስኮት ውስጥ ይጫኑ የ ሰንጠረዥ ምልክት


የ ማስታወሻ ምልክት

እንደ አገባቡ አይነት ይቻላል: ሁሉም ተግባሮች በ እርስዎ በ አሁኑ ዳታቤዝ የ አገባብ ዝርዝር ውስጥ ላይታይ ይችላሉ: ለምሳሌ: የ ግንኙነት ትእዛዝ ለ ግንኙነትን ለ መግለጽ በ ተለያየ ሰንጠረዥ ዝግጁ የ ግንኙነት ዳታቤዝ ውስጥ


እንደ ዳታቤዝ ስርአት አጠቃቀም: እርስዎ የሚከተሉትን የ አገባብ ዝርዝር ማስገቢያዎች ያገኛሉ:

መክፈቻ

ይጠቀሙ የ መክፈቻ ትእዛዝ ለ መክፈት የ ተመረጠውን እቃ በ አዲስ ስራ ውስጥ

ይህ ሰንጠረዥ ክፍት ከሆነ በርካታ ተግባሮች አሉ ዝግጁ ዳታ ለማረም

ግንኙነቱ

ይህ ትእዛዝ የሚከፍተው የ ዳታቤዝ ግንኙነት መስኮት ነው: እርስዎን ግንኙነቱን መግለጽ ያስችሎታል በ ተለያዩ የ ዳታቤዝ ሰንጠረዥ መካከል

አገናኝ መፍጠሪያ

ይህን ትእዛዝ ማስጀመር ይቻላል እቃ ከ ተመረጠ: አገናኝ ከ ተሰየመ "አገናኝ ወደ xxx" (xxx የ እቃውን ስም ይወክላል) በ ቀጥታ በ ተመሳሳይ ዳይሬክቶሪ የ ተመረጠው እቃ በ ነበረበት ውስጥ ይፈጠራል